የህዝብን እምነትና ባህል የሚያጥላላ ስብከት ተቀባይነት የለዉም።

(የአውስትራሊያ ዋቄፈና ማህበር, ሰኔ 6 ቀን 2017) የአውስትራሊያ ዋቄፈና ማህበር ፕሮፌት ሱራፌል ደምሴ በሜይ 30 ቀን 2017 የለቀቁት የስብከት ቪድዮ የኦሮሞን ህዝብ የዋቀፋና እምነት እና የእሬቻ ባህልን የሚያቋሽሽና የሚያጥላላ የተሳሳት ስብከት መሆኑን አስተውለዋል።

cropped-WGA-22.jpgማህበሩ ሰኔ 6 ቀን 2017 ባወጣዉ መግለጫ እንዳስታወቃዉ  ይህ የተሳሳት ስብከት በሰላማዊ ህዝቦች መካከል ተከባብሮ የመኖር መንፈስን የሚያደፈርስም ነው።   ስለእግዝሃብሄር የሚሰብክ አንድ ፕሮፌት የህዝብ እምነት፣ ባህልና ማንነት  ሲያጥላሉ ስንመለከት እጅግ ሀዘን ተሰምቶናል።

የኦሮሞ ህዝብ የተለያዩ እምነት ያለው ህዝብ ሲሆን ለአመታት ከራሱም ሆነ ከሌሎች ህዝቦች ጋር ተከባብሮ የኖረ ህዝብ ነው። የኦሮሞ ህዝብ ለዘመናት የተፈጠሩ ችግሮችን በሰላም የመፍታት ባህል ያለው፣ የሌሎችንም ህዝብ እምነትና ባህል አክባሪ ህዝብ ነው።

ዋቄፈና የሚለዉ ቃል የመጣው ዋቃ ከሚለዉ የኦሮሚኛ የአንድ አምላክ ስም ነዉ። ዋቃ ማለት አንድ አምላክ ለሚለዉ የፈጣሪ ስም የኦሮሚኛ መጠሪያዉ ሲሆን፤ ዋቄፈና ማለት ደግሞ በአንድ አምላክ መገዛትን እና አንድ አምላክ ማመንን ያመላክታል።ዋቄፈና በኦሮሞ ህዝብ ዘንድ ከክርስትና እና ከእስልምና ወደ ኢትዮጵያ መምጣት ቀድሞ የነበረ እምነት ነው።

እሬቻ በብዙ ሚሊዮን የሚቆጠሩ ኦሮሞዎችና ሌሎችም ህዝቦች በአለም አቀፍ ደረጃ እንዲሁም በተለይ በሆረ አርሰዴ / ቢሾፍቱ ለብዙ አመታት ሲያከብር የኖረና ያለ መሆኑ አይካድም። በዛሬው ጊዜ በተለይ ለኦሮሞ ህዝብ እሬቻ እንደ አገር አቀፍ በዓል እየተወሰደ ነው። የትኛውም እምነት ያለው ኦሮሞ እንዲሁም ሌሎችም ህዝቦች ብዙ ቱሪስቶችን ጨምሮ የሚሳተፉበት ትልቅ አለም አቀፍ በአል ሆኗል። እሬቻ የሁሉም ኦሮሞች የማንነት መገለጫ ነው።

ነገር ግን የፕሮፌት ሱራፌል ደምሴ የሜይ 30 ቀን 2017 የተሳሳት ስብከትና አመለካከት በሰላማዊ ህዝቦች መካከል የነበረዉ ተከባብሮ የመኖር መንፈስን የሚያደፈርስ ነው። ይህ የተሳሳት ስብከትና አመለካከት በኦሮሞ ህዝብም ሆነ በሌሎች ሰላም ወዳድ ህዝቦች ዘንድም ተቀባይነት አይኖረውም።

ለዚህም ፕሮፌት ሱራፌል ደምሴ፣

  1. የኦሮሞ ህዝብን ይቅርታ እንዲጠይቁ
  2. ይህንን ጠብ አጫሪ ቪድዮ ከሁሉም ሚዲያ ላይ በአስቸኳይ እንዲያነሱትና
  3.  ይህ ዐይነት የተሳሳት ስብከት እንዳይደገም እንጠይቃለን።

በዚህ አጋጣሚ በእምነት ውስጥ ተደብቆ  የህዝብ እምነት እና ባህል ማንቋሸሽ የእግዝሃብሄር መንገድ እንዳልሆነ  ለማስገንዘብ እንወዳለን።

ሙሉ መግለጫ ከአውስትራሊያ ዋቄፈና ማህበር የተሰጠ መግለጫ

1 Comment on "የህዝብን እምነትና ባህል የሚያጥላላ ስብከት ተቀባይነት የለዉም።"

  1. Hojii gaarii, hojii fedhummaa nagaa ragaa ta’uu ibsa kana irraa hubanna. Jabaadhaa, galatoonaa.

Leave a comment

Your email address will not be published.


*